The Federal Democratic Republic of Ethiopia Financial Intelligence Center(The FDRoE FIC)                                                                                                                        በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል(በኢፌዲሪ ፋደመማ)

1.ጠቅላላ መረጃ

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብንና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት የሀገራችን የደህንነት ስጋት ብቻም ሳይሆን የፋይናንስ ስርዓቱን የተረጋጋ፣ ግልጽነት ያለውና ቀልጣፋ እንዳይሆን የሚያደርግ በመሆኑ የወንጀል ድርጊቱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ በዚህ ረገድ የድርሻዋን ለመወጣት የሚያስችላትን የሕግ ማዕቀፍ በመዘርጋት በይፋ እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች፡፡

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ የወንጀል ድርጊቶቹን በመዋጋት ረገድ የተለያዩ ሕጎችን ያፀደቀ ሲሆን ከዚህ ቀደም በ1997 የወንጀል ሕግ አንቀጽ 684 ብሎም ይህንኑ ድንጋጌ በማስፋት በአዋጅ ቁጥር 657/2001 እንዲካተትና እንዲፀድቅ ካደረገ በኋላ በድጋሚ በአሁኑ ጊዜ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ አዋጅ ቁጥር 780/2005 በማፅደቅ እንዲታወጅ አድርጓል፡፡

ለአዋጁ ተፈፃሚነት እንዲሁም የወንጀል ድርጊቱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ሲባል የፋይናንስ ደህንነት መረጃ ማዕከል አዋጁን መሰረት በማድረግ በደንብ ቁጥር 171 ተቋቁሟል፡፡

2.በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ማለት ምን ማለት ነው?

በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ማለት ማንኛውም ሰው ንብረቱ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው፡-

 • የንብረቱን ሕገ-ወጥ ምንጭ ለመደበቅ ወይም ለመሸፈን ወይም አመንጭውን ወንጀል የፈፀመው ሰው ከህግ ተጠያቂነት እንዲያመልጥ ለማድረግ ንብረቱን የለወጠ ወይም ያስተላለፈ እንደሆነ፤
 • ንብረቱን፣ የንብረቱን ትክክለኛነት፣ ምንጩን፣ ቦታውን፣ ዝውውሩን ወይም የባለቤትነት መብቱን የደበቀ ወይም እንዳይታወቅ ያደረገ እንደሆነ፤
 • ንብረቱን የተረከበ፣ በይዞታው ያደረገ ወይም የተጠቀመ እንደሆነ፤ ማለት ነው፡፡

በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱትን ወንጀሉን የሚያቋቁሙ ተግባራትን በመፈፀም የተሳተፈ፣ ለመፈጸም ያደመ፣ የሞከረ፣ የረዳ፣ ያመቻቸ እንደሆነ ከህግ ተጠያቂነት አይድንም፡፡

ስለዚህ እነዚህን ህገ-ወጥ የወንጀል ድርጊቶች ከወዲሁ መከላከል የሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሀገራዊ ኃላፊት ነው፡፡

የወንጀል ድርጊቶቹን ጥቆማ በማድረግና በማጋለጥ ሁሉም ዜጋ የድርሻውን በመወጣት ሰላም የሰፈነባትና የተረጋጋች ኢትዮጵያን መፍጠር፣ የተጀመረውን ልማት በተያዘለት ዕቅድ የታሰበውን ግብ ለመምታት ያስችለዋል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ የመላው ኢትዮጵያዊያን ማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ዋስትና ለማረጋገጥ አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ያስችላል ማለት ነው፡፡

በሕገ-ወጥ መንገድ የተገኘ ገንዘብ ወይንም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ከፍተኛ ወንጀል ነው። ወንጀሉን በጋራ በመከላከል ሀገራዊ ኃላፊነታችንን እንወጣ!!

በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት የመሠወሪያ ዘዴዎች

 1. የመጀመሪያው የመሰወሪያ ዘዴ (Placement)
 2. ይህ የመሰወሪያ ደረጃ በህገ-ወጥ መንገድ ያገኘውን ገንዘብ በፋይናንስ ስርዓት ውስጥ የሚያስተዋውቅበት/የሚያስገባበት/ ደረጃ ነው፡፡ አፈፃፀሙ ገንዘቡን በተለያየ ቦታ በመከፋፈል ቀስ በቀስ የባንክ ሂሳብ ከፍቶ ተቀማጭ በማድረግ ወይም ከሌሎች ግለሰቦችና ተቋማት ቼኮችን ወይም ሌሎች በምንዛሬ ሰነዶችን በመግዛት ከባንክ ክፍያ ተቀብሎ በሌላ ሂሳብ ውስጥ በማስቀመጥ ነው፡፡
 3. ሁለተኛው የመሰወሪያ ዘዴ(Layering)
 4. በዚህ ደረጃ ገንዘቡን ከሕገ-ወጥ ምንጩ ለማራቅ በተከታታይ የማንቀሳቀስ ተግባር ይፈፀማል፡፡ ይህም የሚከናወነው በተለያዩ ባንኮች ገንዘቡን በመቀያየርና እንደ አስፈላጊነቱ በተለያዩ ሀገራት እንዲዘዋወር በማድረግ ነው፡፡ በተለይም ይህን ሕገ-ወጥ ድርጊት ለመከላከል ስርዓት ባልዘረጉ ወይም ያልተጠናከረ ስርዓት ያላቸውን ሀገራት መጠቀም ይመርጣሉ፡፡ ገንዘቡንም ለዕቃ ወይም ለተሰጠ አገልግሎት የተፈፀመ ክፍያ አድርገው ይቀበላሉ፡፡
 5. ሦስተኛው የመሰወሪያ ዘዴ(Integration)
 6. በሁለት የመጀመሪያ ዘዴዎች በስኬት ካለፉ በኋላ በማሸጋገር ገንዘቡን እንደገና ሕጋዊ ገበያ ውስጥ ያስገባሉ፡፡ ገንዘቡንም በሪልስቴት፣ ውድ ዕቃዎችን በመግዛት ወይም ሼሮችን በመግዛት ኢንቨስት ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡ ይህን ሁሉ ተግባር የሚያደርጉት የኢኮኖሚ ትርፍ ለማግኘት ወይም ላለመክሰር ሳይሆን በወንጀል ተግባር የቆሸሸውን ገንዘብ ማጽዳት የህልውና ጉዳይ ስለሚሆንባቸው ነው፡፡

በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት የመሠወሪያ ዘዴዎች በምስል ሲገለጽ ከላይ የተመለከተውን ይመስላል፡፡

3.ሽብርተኛ ማለት ምን ማለት ነው?

ሽብርተኛ ማለት ፡-

 • በማንኛውም መንገድ በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ሕግን በመጣስና በራሱ ፈቃድ የሽብርተኝነት ድርጊት የሚፈፅም ወይም ለመፈፀም የሚሞክር፣
 • በሽብርተኝነት ድርጊት አባሪነት የሚሳተፍ፤
 • ሌሎች ሰዎች በሽብርተኝነት ድርጊት እንዲሳተፉ የሚያደራጅ ወይም አመራር የሚሰጥ ወይም፤
 • የሚያደርገው አስተዋፅኦ ሽብርተኝነትን እንዲስፋፋ በመፈለግ ወይም ቡድኑ የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈፀም ማሰቡን እያወቀ ለጋራ ዓላማ በቡድን የተሰባሰቡ ሰዎች ለሚፈፅሙት የሽብርተኝነት ድርጊት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ማንኛውም ቡድን ነው፡፡


4.የሽብርተኝነት ድርጊት ምንነት

 • ሽብርተኝነት ማለት በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌላ ቦታ የተፈፀመ እ.ኤ.አ. በ1999 ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን ለመከላከል በወጣው ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን አባሪ ከሆኑት ስምምነቶች በአንዱ የተፈፃሚነት ወሰንና ትርጓሜዎች የሚሸፈን የወንጀል ድርጊት ነው፡፡
 • ዝርዝሩን International Convention for the Suppression of the -Financing- of Terrorism 1999 ብለው ጎግል ኢንተርኔት ላይ በመግባት ሀያ ስምንቱንም አንቀጾችን በአንድ መመልከት ይችላሉ፡፡ ይህን በማድረግ ሀገራዊ ኃላፊነትዎን ይወጡ፡፡
 • በኢትዮጵያ ውስጥም ሆ በሌላ ቦታ የተፈፀመ ከድርጊቱ ባህሪ ወይም ይዘት ሲታይ ህብረተሰቡን ለማስፈራራት ወይም መንግሥትን ወይም ዓለም አቀፍ ድርጅት አንድን ድርጊት እንዲፈፀም ወይም እንዳይፈፀም የማስገደድ ዓላማ ኖሮት ሲቪል ከሆነ የኅበረተሰቡ አባል ላይ ወይም በውጊያ ሁኔታ ውስጥ ተሳታፊ ባልሆነ ማንኛውም ሌላ ሰው ላይ ሞትን ወይም ከባድ የአካል ጉዳት ለማድረስ ታስቦ የተፈፀመ ሌላ ድርጊት የሽብርተኝነት ድርጊት ይባላል፡፡

5.የሽብርተኛ ድርጅት ምንነት

ይህ ማለት በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌላ ቦታ የሚገኝ ወይም የሚንቀሳቀስ ሆኖ፡-
 1. በማንኛውም መንገድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሕግ በመጣስና በራሱ ፈቃድ የሽብርተኝነት ድርጊት የሚፈፅም ወይም ለመፈፀም የሚሞክር፤
 2. በሽብርተኝነት ድርጊት በአባሪነት የሚሳተፍ፤
 3. ሌሎች ሰዎች በሽብርተኝነት ድርጊት እንዲሳተፉ የሚያደራጅ ወይም አመራር የሚሰጥ፤
 4. የሚያደርገው አስተዋፅኦ ሽብርተኝነትን እንዲስፋፋ በመፈለግ ወይም ቡድኑ የሽብርተኝነት ድርጊት ለመፈፀም ማሰቡን እያወቀ ለጋራ ዓላማ በቡድን የተሰባሰቡ ሰዎች የሚፈፅሙት የሽብርተኝነት ድርጊት አስተዋፅኦ የሚያደርግ ማንኛውም ቡድን ነው፡፤
 5. በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 ድንጋጌዎች መሠረት በሽብርተኝነት የተሰየመ ድርጅት ነው፡፡
የፀረ- ሽብርተኝነት አዋጁን በዝርዝር ለማየት Ethiopian Anti-Terrorism Proclamation No. 652/2009 ብለው ኢንተርኔት ላይ በመግባት ያገኙታል፡፡

ለቀጣይ የፀረ-ሽብርተኝነት ትግሉ ትልቅ አቅም ፈጥረን የተረጋጋችና ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያን እንገንባ፣

ሀገራችን አሁን የተያያዘችውን የልማትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እውን በማድረግ የወደፊት የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ልማት ማንነታችንን እናረጋግጥ፣

በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ማኅበራዊ ጉዳዮች ተፅዕኖ መፍጠር የምትችል ኢትዮጵያን እንፍጠር፣

ይህንን እውን ለማድረግ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን የሚፀየፍ ማኅበረሰብ መገንባት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው፡፡

ሽብርተኝነትን የመርጃ ገንዘብ ምንጮች

የገንዘብ ምንጩ በርካታ ቢሆንም ዋና ዋና የሽብርተኝነት መርጃ ገንዘብ ምንጮች ሁለት መንገዶች ናቸው፡፡
 1. ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚሰበሰብ ገንዘብ
  • ከሰብዓዊ እርዳታ የሚሰበሰብ ገንዘብ (Humanitarian Organizations)
  • በግል የሚደረግ ዕርዳታ (Private Donation)
  • ከህትመቶች ወይም ከተለያዩ ዕቃዎች ሽያጭ በሚገኝ ገንዘብ (Sales of Publications or Merchandise)
  • ለኮንፈረንሶች ወይም ለተለያዩ አስተምህሮቶች በመስጠት የሚገኝ ገንዘብ (Civic Associations)
 2. ሕገ-ወጥ በሆ መንገድ የሚሰበሰብ ገንዘብ
  • ሕገ-ወጥ ንግድ በማካሄድ
  • ሕገ-ወጥ የጦር መሳሪያና የመድሐኒት ሽያጭ በማካሄድ የሚገኝ ገንዘብ
  • ጠለፋ በማካሄድ የሚገኝ ገንዘብ (Kidnapping)
  • በስርቆት የሚገኝ ገንዘብ (Theft)
  • በማስፈራራት የሚገኝ ገንዘብ (Extortions
  • በማጭበርበር የሚገኝ ገንዘብ (Fraud)
  • በኮንትሮባንድ ንግድ የሚገኝ ገንዘብ ወይም ንብረት (Smuggling)
  • በኃይል ጥቃት የሚገኝ ገንዘብ (Assaults) እነኚህ ከብዙ በጥቂቱ ተጠቃሽ ናቸው፡፡

6.የወንጀል ቡድን ማለት ምን ማለት ነው

የወንጀል ቡድን ማለት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የገንዘብ ወይም የሌላ ቁሳዊ ጥቅም በማግኘት ዓላማ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ከባድ ወንጀሎችን ለመፈፀም የተሰባሰቡና ተቀናጅተው የሚንቀሳቀሱ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎችን የያዘ ቡድን ነው፡፡

ይህ የወንጀል ድርጊት የሚያስከትላቸው ጉዳዮች፡- ሕዝቡ በሀገሪቱ የፍትሕ ስርዓት እንዳይተማመን ስለሚያደርግ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ (Social & political Crisis) ይፈጥራል፤

 • የበርካታ የፋይናንስ ተቋማት ለወንጀል ድርጊት ተጋላጭና መፈልፈያ የመሆን፤
 • ያልተጠበቀ የገንዘብ ፍላጎት መጨመር፤
 • ሕጋዊ ግብይቶች መበከል፤
 • የዓለም አቀፍ የፖለቲካ ፍሰት አለመረጋጋት፤
 • የውጭ ምንዛሬ ተመን በየጊዜው መዋዠቅ፤
 • የተሻለና የተረጋጋ የፋይናንስ ስርዓት ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ የኢንቨስተሮች ፍልሰት፤

በአጠቃላይ በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች፣ በፋይናንስ ስርዓትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ፖሊሲ አፈፃፀም ላይ ከፍተኛ ቀውስ ያስከትላል፡፡ ይህ አይነቱ ቀውስ ደግሞ በቀላሉ ሊጠገን የሚችል አይደለም፡፡ በተለይም ደግሞ የኪራይ ሰብሳቢነትና የብልሹ አሰራር ስር በሰደደባቸው ሀገራት ስር ነቀል የሆነ የለውጥ አስተዳደርንና የአዳዲስ አሠራርን ተግባራዊ ማድረግን ከመጠየቁም አልፎ የሚያስከፍለው መስዋትነት ቀላል የሚባል አይደለም፡፡

ምቹ የመታገያ መሳሪያዎችን አሟጦ መጠቀም ግን አማራጭ የሌለው መፍትሔ ነው፡፡ ለምሳሌ በኢትዮጵያ የወጣውን አዋጅ 780/2005ን ተግባዊ በማድረግ የህግ የበላይነትን በማረጋገጥ ችግሩ ስር ሳይሰድ መግታትና መቆጣጠር ይቻላል፡፡

Terrorist attack in Tgray Hotel at Addis Ababa.

ሽብርተኝትን በገንዘብ መርዳት ከፍተኛ ወንጀል ነው። ወንጀሉን በጋራ በመከላከልና በመቆጣጠር ጤናማ የተረጋጋና ቀልጣፋ የፋይናንስ ስርዓት በማስቀጠል ሀገራችን እያስመዘገበች ያለውን ፈጣን የልማትና የህዳሴ ጉዞ ያለምንም ስጋት በማስቀጠል ራዕያችንን ዕውን እናደርጋለን!!


Ethiopia

Ethiopia, officially known as the Federal Democratic Republic of Ethiopia, is a sovereign state located in the Horn of Africa. It shares a border with Eritrea to the north and northeast, Djibouti and Somalia to the east, Sudan and South Sudan to the west, and Kenya to the south. With nearly 100 million inhabitants, Ethiopia is the most populous landlocked country in the world, as well as the second-most populous nation on the African continent after Nigeria. It occupies a total area of 1,100,000 square kilometers’ (420,000 sq mi), and its capital and largest city is Addis Ababa. Some of the oldest evidence for anatomically modern humans has been found in Ethiopia, which is widely considered the region from which modern humans first set out for the Middle East and places beyond. Ethiopia's ancient Ge'ez script, also known as Ethiopic, is one of the oldest alphabets still in use in the world. The Ethiopian calendar, which is approximately seven years and three months behind the Gregorian calendar, co-exists alongside the Borana calendar. Ethiopia is the place of origin for the coffee bean which originated from the place called Kefa (which was one of the 14 provinces in the old Ethiopian administration). It is a land of natural contrasts, with its vast fertile West, jungles, and numerous rivers, and the world's hottest settlement of Dallol in its north. The Ethiopian Highlands are Africa's largest continuous mountain ranges, and Sof Omar Caves contain Africa's largest cave. Ethiopia has the most UNESCO World Heritage Sites in Africa. Ethiopia is one of the founding members of the UN, the Group of 24 (G-24), the Non-Aligned Movement, G-77 and the Organisation of African Unity. Ethiopia's capital city Addis Ababa serves as the headquarters of the African Union, the Pan African Chamber of Commerce and Industry, the United Nations Economic Commission for Africa, African Aviation Training HQ, the African Standby Force, and much of the global NGOs focused on Africa. In the 1970s and 1980s, Map of Ethiopia. read more….

FATF Recommendations

  The FATF Recommendations set out a comprehensive and consistent framework of measures which countries should implement in order to combat money laundering and terrorist financing, as well as the financing of proliferation of weapons of mass destruction. Countries have diverse legal, administrative and operational frameworks and different financial systems, and so cannot all take identical measures to counter these threats. The FATF Recommendations, therefore, set an international standard, which countries should implement through measures adapted to their particular circumstances. The FATF Recommendations set out the essential measures that countries should have in place to:
 1. identify the risks, and develop policies and domestic coordination;
 2. pursue money laundering, terrorist financing and the financing of proliferation;
 3. apply preventive measures for the financial sector and other designated sectors;
 4. establish powers and responsibilities for the competent authorities (e.g., investigative, law enforcement and supervisory authorities) and other institutional measures;
 5. enhance the transparency and availability of beneficial ownership information of legal persons and arrangements; and
 6. facilitate international cooperation.
 7. The original FATF Forty Recommendations were drawn up in 1990 as an initiative to combat the misuse of financial systems by persons laundering drug money. Read more....